የጨረታ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በተጠቀሰው ጨረታ ቁጥር በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

DIST 3/2000   Street Lighting Materials

ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራ በጨረታ ሰነዱ ላይ የተቀመጠውን የስራ ልምድ የሚያሟላ ብቃት ያለው የንግድ ድርጅት የተጠቀሰውን ዕቃ ለማቅረብ መወዳደር ይችላል፡፡

ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ) በመክፈል ከዚህ በታች በተጠቀሰው አድራሻ ማግኘት ይችላሉ፡፡

                  ፒያሳ ደጎል አደባባይ የዲስትሪቢዩሽን አስተዳደር እና ፋይናንስ

                  ስልክ ቁጥር 011-1-575596

የጨረታ ሰነዶቹን ከመጋቢት 22 ቀን 2000 ዓ.ም. ጀምሮ ማግኘት ይችላሉ፡፡

ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉበት የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ወረቀት፣እንዲሁም የገንዘብ ሚኒስቴር የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡

ተጫራቾች የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ማለትም ሲፒኦ ብቻ አንድ መቶ ሺ ብር (100,000.00) ማስያዝ አለባቸው፡፡

ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን “DIST 3/2000 Supply & Delivery of Street Lighting Materials” የሚል ምልክት በማድረግ እስከ ሚያዝያ 22 ቀን 2000 ዓ.ም. ከቀኑ 5፡00 ሰዓት በፊት ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ ማስገባት አለባቸው፡፡

ጨረታው ሚያዝያ 22 ቀን 2000 ዓ.ም. ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሜክሲኮ አደባባይ በመብራት ኃይል ክበብ ግቢ ይከፈታል፡፡

ተጫራቾች የመጫረቻ ዋጋቸውን በጨረታ ሰነዱ ላይ በተጠየቀው መሰረት ማቅረብ አለባቸው፡፡

ኮርፖሬሽኑ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

    Federal Democratic Republic of Ethiopia

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን

ETHIOPIAN ELECTRIC POWER CORPORATION