Home

News

Company Profile

Brief

Organization Chart

Power SDP

Tender


Tariff Level


Vacancy

Costumer Service

Video

 

Addis Ababa, Ethiopia
Visitor Feb. 27, 2007

የጨረታ ማስታወቂያ

Monday, 22 September 2008

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በተጠቀሰው ጨረታ ቁጥር በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

DIST 2/2001

         Lot 1 XLPE LV insulated wire & 0.6/1 kV Cables

         Lot 2 ABC Cables

ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራ የሃገር  ውስጥ አምራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ የተቀመጠውን የስራ ልምድ የሚያሟላ ብቃት ያለው አምራች ድርጅት የተጠቀሰውን ዕቃ ለማቅረብ መወዳደር ይችላል፡፡

ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ) በአንድ Lot በመክፈል ከዚህ በታች በተጠቀሰው አድራሻ ማግኘት ይችላሉ፡፡

                                          ፒያሳ ደጎል አደባባይ

                              የዲስትሪቢዩሽን አስተዳደር እና ፋይናንስ

                                      ስልክ ቁጥር 011-1-575596

 

የጨረታ ሰነዶቹን ከመስከረም 12 ቀን 2001 ዓ.ም. ጀምሮ ማግኘት ይችላሉ፡፡ 

ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉበት የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ወረቀት፣እንዲሁም የገንዘብ ሚኒስቴር የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡

ተጫራቾች የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ማለትም ሲፒኦ  ሰባት መቶ ሺ ብር (700,000.00 ለ Lot 1) እና አምስት መቶ ሺ ብር (500,000.00 ለ Lot 2) ማስያዝ አለባቸው፡፡

ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን “DIST 2/2001 Supply & Delivery of

      Lot 1 XLPE LV insulated wire & 0.6/1 kV Cables

         Lot 2 ABC Cables

የሚል ምልክት በማድረግ እስከ ጥቅምት 12 ቀን 2001 ዓ.ም. ከቀኑ 5፡00 ሰዓት በፊት ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ ማስገባት አለባቸው፡፡

ጨረታው ጥቅምት 12 ቀን 2001 ዓ.ም. ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሜክሲኮ አደባባይ በመብራት ኃይል ክበብ ግቢ ይከፈታል፡፡

ተጫራቾች የመጫረቻ ዋጋቸውን በጨረታ ሰነዱ ላይ በተጠየቀው መሰረት ማቅረብ አለባቸው፡፡

ኮርፖሬሽኑ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን

                                          Copyright © 2002- 2008 Ethiopian Electric Power Corporation (EEPCo).
                                                        All rights reserved.