ራዕይ
“በአገራችን ለሚገኝ ለሁሉም ነዋሪ ዓለም አቀፍ ጥራትና ብቃት ያለው
የኤሌክትሪ,ክ ኃይል አገልግሎት መስጠትና ተወዳዳሪ የኤሌክትሪክ
ኤክስፖርተር እንዱስትሪ መሆን“
ተልዕኮ
“በዘርፉ ያለውን ልምድ በማጎልበት የኅብረተሰቡን ኢኮኖሚያዊ ዕድገት፣
አካባቢያዊ ጥበቃና እንክብካቤ ባገናዘበ መልኩ ብቁ፣ አስተማማኝና የጥራት
ደረጃውን የጠበቀ የኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት፣ የማስተላለፍ የማሰራጨትና
የመሸጥ አገልግሎት መስጠት”
አገራችን ባለፉት አምስት ዓመታት ፈጣን ኢኮኖሚያዊ፣ ማኀበራዊ ዕድገትን
በማረጋገጥና በማፋጠን፣ ዲሞክራሲያዊና ልማታዊ መንግስትን እውን በማድረግ
ረገድ በታሪካችን ታይቶ የማይታወቅ ለውጥና ድል አስመዝግባለች፡፡
ከዚህም አኳያ ይህ የኢኮኖሚ ዕድገት ወደፊት ዘላቂ ሆኖ ሲቀጥል በአጭር ጊዜ
ውስጥ የምግብ ዋስትናን በአገር፣ በአካባቢና በቤተሰብ ደረጃ ለማረጋገጥና
በቀጣይም ሩቅ በማይባል ጊዜ ውስጥ ድኸነትን ለማስወገድ እንደሚያስችል
ታምኗል፡፡
በመሆኑም በአገራችን የኢኮኖሚ ዕድገትን በማፋጠንና ዕድገቱም ቀጣይነት
እንዲኖረው በማስቻል፣ ሕዝቡ በየደረጃው ተጠቃሚ የሚሆንበትንና ቢያንስ
የምዕተ ዓመቱን የልማት ግቦች ለማሳካት የሚያስችሉ አስተማማኝ የልማት
ውጤቶች እንዲኖር ለማድረግ፡-
በአገራችን ባለፉት ተከታታይ ዓመታት የመጀመሪያው የ5 ዓመት የልማት
ዕቅድ ትግበራ ዘመን አጠቃላይ የአገሪቱ ኢኮኖሚ በአማካይ በዓመት ከ11 በመቶ
በላይ ዕድገት አስመዝግቧል፡፡
ስለሆነም ይኸው የእድገት ምጣኔ በዚሁ ከቀጠለ የምዕተ ዓመቱን የልማት ግቦች
ከማሳካት ባሻገር እ.ኤ.አ ከ2025 በኋላ መካከለኛ ገቢ ካላቸው አገሮች ተርታ
ለመሰለፍ የተቀመጠውን ራዕይ ዕውን ለማድረግ እንደሚቻል ያመለክታል፤
በመሠረታዊ የኢኮኖሚ የዕድገት አማራጭ ኢኮኖሚው ላለፉት ስድስት ዓመታት
በየዓመቱ በአማካይ ያስመዘገበውን የ11 በመቶ በላይ ዕድገት ቀጣይነት
ማረጋገጥ፤
በከፍተኛ የኢኮኖሚ የዕድገት አማራጭ የግብርና
ምርትና አጠቃላይ ኢኮኖሚውን በ2002 ከነበረበት እስከ በ2007 ዓ.ም እጥፍ
ማሳደግና ይህንን ለማሳካት ኢኮኖሚውን በየዓመቱ በአማካይ 15 በመቶ ያህል
ማሳደግ፣ የኢንዱስትሪውን ዕድገት በማፋጠን ዘርፉ በኢኮኖሚው ውስጥ የመሪነት
ሚናውን ሊረከብ የሚችልባቸውን ሥራዎች ማጠናቀቅ፤
የሕዝብ ብዛት ዕድገትም በአማካይ ከ2.4 በመቶ እንደማይበልጥ ግብ ተቀምጧል፤
በዕቅዱ ዘመን መጨረሻም (2007) ከድኸነት ወለል በታች በሚኖረው ሕዝብ
ምጣኔም በ1997 ዓ.ም ከነበረበት 38.7 በመቶ ወደ 22 በመቶ ዝቅ እንደሚል
ግብ ተጥሏል፤
የትምህርትና የጤና አገልግሎት ሽፋንን በመጨመርና ጥራትን በማረጋገጥ ላይ
የተመሰረተ ማኀበራዊ ልማት በማካሄድ የሚሊኒየም ልማት ማኀበራዊ ግቦችን
ለማሳካት መንግስት የአምስት ዓመት የዕድገትና የትራንስፎርሜሸን ዕቅድ
ተነድፏል፤
በተያዘው ዓላማ ለኢንቨስትመንት በተፈጠረው ምቹ ሁኔታ የኢንዱስትሪና
የአገልግሎት ሰጪው ሴክተሩ በከፍተኛ ደረጃ እያደገ በመምጣቱ ባለፉት ዓመታት
ኢኮኖሚው ባደገበት በ11 በመቶ የአገር ውስጥ ምርት (GDP) ዕድገት የ24
በመቶ የኃይል ፍላጎት ዕድገትና በከፍተኛ 15 በመቶ የአገር ውስጥ ምርት
ዕድገት ደግሞ 32 በመቶ የኃይል ፍላጎት ዕድገት ሊከሰት እንደሚችል በመተንበዩ
የኃይል አቅርቦትና ፍላጎት ልዩነት እንዳይታይ ከፍተኛ የኃይል ልማት ሥሪዋች
በዕቅድ ተይዘዋል፡፡
የኃይል ልማትን በአገር ውስጥ አቅም ማከናወን በርካታ ጠቀሜታዎች እንዳሉት
የታወቀ ሲሆን በዋናነት በከፍተኛ ደረጃ የውጪ ምንዛሪ ፍላጎትን የሚቀንስ
ሲሆን በአገራችን ገና ያልተነካውን ዕምቅ ታዳሽ የኃይል ምንጭ ልማት በስፋት
ለማካሄድና አገር ውስጥ ያሉት ኩባንያዎች ከአገር ውስጥ ወጣ ብለው እንዲሳተፉ
እድልን ሊፈጠራላቸው የሚችልበት ሁኔታም ተመቻችቷል፡፡
ኮርፖሬሽናችን በቀጣይ የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዓመታት ብሎም
ከ2004 በጀት ዓመት ጀምሮ የሚተገበር ሶስት ዓላማዎች ላይ መሰረት ተደርጎ
እንዲሠራ አጠቃላይ የኃይል ልማት ዕቅድ ጸድቋል፡፡
ከዚህም አኳያ በአንደኛ ደረጃ ኮርፖሬሽኑ የተፈጠረውን ዕድገትና በቀጣይ
አመታቶች የሚፈጠረውንም በመጨመር በተገቢው መንገድ ማስተናገድ
የሚችልና የዓለም አቀፍ የፓወር ሴክተር ዕድገትን ተከትሎ ሊሄድ እንዲችል
ኮርፖሬሽኑን እንደገና የማደራጀት ሥራ መሥራት ሲሆን፣
በሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ደግሞ በማመንጨት፣ በማስተላለፍ፣
በማሰራጨት፣ አገራችን በኃይል አቅርቦቱ ሥር ነቀል ለውጥ በማምጣት ከራሷ
ፍጆታ ተርፋ በምስራቅ አፍሪካ የታዳሽ የኃይል ምንጪ ማዕከል እንድትሆን
ማድረግ፤
ሶስተኛው ደግሞ እነዚህን ከላይ የተጠቀሱትን ሥራዎች በአገር ውስጥ አቅም
የሚከናወኑበትን መንገድ ማመቻቸትና በራስ ኃይልም ጭምር ማከናወን ናቸው፡፡
በተለይ ከላይ በሁለተኛ በሶስተኛው ግብ የተቀመጡትን ለማከናወን ይረዳ ዘንድ
በማመንጨት፣ በማስተላለፍ የሥራ እንቅስቃሴዎች ግብአት አምራቾችን
መንግስት በአንድ ጥላ ስር የሚገኙበትን ሁኔታ በማመቻቸቱ ከብረታ ብረትና
ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሸን ጋር በጋራ የመስራቱን ሂደት አጠናክሮ በማስቀጠል እና
ብሎም በራስ ኃይል የሚከናወኑትንም ሥራዎችንም በከፈተኛ ተነሳሽነት
ማከናወን፤
በዋናነት ይህን ሥራ ትኩረት ሰጥቶ ለማከናወን ይቻል ዘንድ ከየሥራ ሂደቶች
በየዘርፉ ሊያስፈጽሙ የሚችሉ ባለሙያዎች ተወጣጥተው ሥራው እየተከናወነ
ይገኛል፡፡
ከዚህ በመነሳትም ኮርፖሬሽኑ እንደገና በማደራጀት፣ የኃይል ልማትን ማስፋፋትና
የአገር ውስጥ አስተዋጽዖን በኮንስትራክሽንም ሆነ በግብአት ምርት ከፍ ለማድረግ
በአምስት ዓመቱ መሪ ዕቅድ ውስጥ በሁለተኛው ዓመት የሚከናወኑትን ሥራዎች
የመሪ ዕቅድ አዘጋጅቷል፡፡
ኢትዮጵያ የሕዝቦቿን መጠነ ሰፊ ችግር ለመቅረፍ እንቅስቃሴ ከጀመረች ሁለት
አስርተ ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ በእነዚህ ዓመታት ዘላቂ መፍትሔ ማምጣት
የሚቻልበትን የስትራቴጂክ ዕቅድ በመንደፍ የሁሉም ዘርፍ መ/ቤቶች ግባቸውን
በማቀድ ለዓላማው መሳካት በርካታ ሥራዎችን በማከናወን ላይ ናቸው፡፡
ባለፉት የስትራተጂክ ዓመታት የተገኙትን ውጤቶችና ግብዓቶች መሠረት
በማድረግ ለአምስት ዓመታት የሚያገለግል የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ
ተነድፎ በመጀመሪያው በ2003 የበጀት ዓመት መጠነ ሰፊ ሥራዎች በመሥራት
የተጀመረው ጉዞ ቀጣይነት እንዲኖረው ሁሉም የበኩሉን አስተዋጽዖ እያደረገ
ይገኛል፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን ከ2003 - 2007 ዓ.ም የሚያገለግል
ከዋናው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ጋር የተጣጣመ የስትራተጂክ ዕቅድ
ነድፎ በመንቀሳቀስ ላይ ሲሆን በመጀመሪያው የበጀት ዓመት፡-
ባለፈው የስትራተጂክ ዘመን ተጀምረው የነበሩ
የኃይል ማመንጫ ጣቢያዎች ቀጣይ ሥራዎች መካከል አንዱ ሊጠናቀቅ
ችሏል፡፡
የማስተላለፊያ መስመርና ማከፋፈያ ጣቢያዎች ግንባታ ሥራ በማጠናቀቅ
ለአገልግሎት እንዲበቁ ተደርጓል፡፡
ኤሌክትሪክ እንዲያገኙ ግንባታቸው የተጀመሩ በርካታ የገጠር ከተሞችና
መንደሮች የማጠናቀቅ ሥራ ተከናውኗል፡፡
የአዲስ አበባና አካባቢዋ የምድር ውስጥ የማከፋፈያ መስመሮች የመልሶ
ግንባታ ሥራ ተጠናቋል