ግንባታቸው ተጀምሮ በመከናወን ላይ የሚገኙ
የኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጫ ጣቢያዎች
የማስተላለፊያ መስመሮችና የማከፋፈያ ጣቢያዎች
በአገር አቀፍ ኤሌክትሪክ ኃይል የማድረስ ሥራዎች
የኤሌክትሪክ ኃይል ማከፋፈያ መስመሮችና የመልሶ ግንባታ ሥራዎች
በሁሉም የኮርፖሬሽኑ ሪጅኖች እየተከናወኑ የሚገኙ
በመደበኛና አገልግሎት ሰጪ ሥራዎች እየተከናወኑ የነበሩ ሲሆን በነዚህ
ዓመትም በኮርፖሬሽን ደረጃ የተቀመጡ ቁልፍ ተግባራት በ2004 በጀት ዓመት
መሪ ዕቅድ ተዘጋጅቷል፡፡
ዓላማ
የሀገሪቱን የዕድገት አቅጣጫ አስተማማኝና ቀጣይነት እንዲኖረው ለማድረግ
የኃይል ዘርፉን አቅርቦት አጠናክሮ በመስራት የሀገሪቱን የኃይል ፍላጎት ማሳካት
ይህንን ዓላማ ከግብ ለማድረስ ኮርፖሬሽኑ በሦስት ዐብየት ዓላማዎች ላይ
ተመስርቶ የቀጣይ አምስት ዓመት ስትራተጂውን ነድፏል፡፡
እነዚህም፡-
ዓላማ
1፡ እያደገ ከመጣው የኃይል ፍላጎት አቅርቦት
ዕድገት ጋር
የተጣጣመ እንዲሆን ኮርፖሬሽኑን እንደገና ማደራጀት (Re-Organize)
ማድረግ፤ በዚህ ዓላማ ዙሪያ ኮርፖሬሽኑን እንደገና የማደራጀት ሥራ
በ2004 በጀት ዓመትም የሚከናወን ወሳኝ ተግባር ነው፤
ዓላማ 2፡ ኢትዮጵያ በኃይል አቅርቦት ሥር ነቀል ለውጥ በማካሄድ ከራሷ ፍጆታ
ተርፋ በምሥራቅ አፍሪካ የታዳሽ የኃይል ምንጭ ማዕከል እንድትሆን
ማድረግ
ዓላማ 3፡ በአገር ውስጥ አምራቾችና ኮንትራት
ተቋራጮችን ግንባታዎችን ማከናወን
አምራቾች
ከዚህ ቀደም በኮርፖሬሽኑ ይኬድበት የነበረውን 80 በመቶ የውጭ ምንዛሪ
አስፈላጊ ግብአቶችን አገር ውስጥ በማምረት ወደ 20 በመቶ ዝቅ ለማድረግ
እንዲቻል መንግሥት ይህንን ግምት ውስጥ በማስገባት የብረታ ብረትና
ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽንን በማቋቋም ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን
ጋር በጋራ ለመሥራት መርሐግብር ተዘጋጅቷል፡፡ ይህ መሪ ዕቅድም በዚህ
ዓመት መሠረት ይተገበራል፡፡ በዚህም መሠረት በኃይል ማመንጫ፣
ማስተላለፊያና ማከፋፈያ አዳዲስ ሥራዎችና ለጥገና የሚያስፈልጉ ግብአቶችን
ለማምረት ዝርዝር መርሐግብር ተዘጋጅቷል::
ኮንትራክተሮች
ሀገር-በቀል ኮንትራክተሮችን በማደራጀትና በሀገር-አቀፍ ኤሌክትሪክ የማድረስ
መርሀ-ግብር ውስጥ ኮንትራክተሮች በማካተትና በየአስተዳደር ክልሎች ከሙያና
ቴክኒክ ት/ቤት የተመረቁ ተማሪዎችን ስልጠና በመስጠት ሰፊ ሥራ እንዲሠራ
ተደርጓል፡፡
ድርጅታዊ ዳሰሳ
ኮርፖሬሽኑ ከጊዜ ወደ ጊዜ አገልግሎቱን እያስፋፋና አቅሙን እያጎለበት
ለመምጣቱ የአለፉት አምስት ዓመታት የተመዘገቡ ውጤቶች ህያው
መረጋገጫዎች ናቸው፡፡
የውስጥ አቅምን አጠናክሮ በራስ ኃይል በመታገዝ እስከ
500 ኪቮ ድረስ
ለማጥናትና ዲዛይን በመንደፍና እስከ
400 ኪ.ቮ ድረስ የከፍተኛ ኃይል
ማስተላለፊያ መስመሮችን መዘርጋት መቻሉ ለወደፊት እንቅስቃሴ ተስፋ ሰጭ
ነው፡፡ በሚያከናውናቸው መጠነ
-
ሰፊ የግንባታ ሥራዎች ሀገር-በቀል
ኮንትራክተሮችና አምራቾች መሳተፋቸው ጠንካራ አቅም ከመፍጠር ባሻገር
ኮርፖሬሽኑንም የጊዜ፣ የአስተዳደርና የሰው ኃይል መባከን ለማስቀረት የበኩሉን
አስተዋፅኦ አበርክቷል፡፡
በመጪው ዓመትም በኃይል ማመንጫ
፣ ማስተላለፊያና
ማከፋፋያ
መስመሮችና ጣቢያዎች የአገር አቀፍ ኤሌክትሪክ ማስፋፊያ መርሀ-ግብር
ለደንበኞች አስተማማኝ የኤሌክትሪክ አቅርቦት በብቃትና በአስተማማኝነት
ማቅረብን ያካትታል፡፡
የማስፈጸም አቅም ግንባታ
1. የኮርፖሬሽኑን የ25 ዓመት ማስተር ፕላን ከስትራተጂክ ዕቅድ ጋር ወቅታዊ
ማድረግ
2. ምርታማነትን ለማሳደግ ብቁ የሰው ኃይል ማፍራት
3. ምቹና ጤናማ የሆነ የሥራ አካባቢ መፍጠር
4. የተሻለ የሴቶች ተሳታፊነትንና ተጠቃሚነትን መፍጠር
5. የኤች አይ ቪ/ኤድስ ስርጭትን ለመግታት የተከናወኑ ሥራዎች
6. ከሙስና የፀዳ፣ ኃላፊነትን በአግባቡ ሊወጣ የሚችልና የሕዝብ አገልጋይነትን
ተላብሶ ለደንበኞች አገልግሎት ትኩረት ሰጥቶ ሊሠራ የሚችል ሠራተኛ
መፍጠር
7. ደረጃውን የተጠበቀ የኦዲት ክትትል በማካሄድ በኮርፖሬሽኑ የተጠናከረ
የውስጥ ቁጥጥር እንዲኖር በማድረግ ሥራዎች አዋጅን፣ መመሪያንና
ደንብን አክብረው እንዲከናወኑ ማድረግ
8. በሕግ አገልግሎት ምክርና አስተያየት መሠረት መልካም አስተዳደር
እንዲፈጠርና እንዲሰፍን ማድረግ፤የሕግ የበላይነት የተከበረበት የኮርፖሬሽን
ፋይናንስ፣ ንብረትና ጥቅሞች ሥራ ላይ እንዲውል ማድረግ
9. ለማርኬቲንግና ሽያጭ፤ለዲስትሪቡሽንና ለሀገር አቀፍ ኤሌክትሪክ አቀርቦት
ፐሮግራም አገልገሎት የሚውሉ
275,000 የዕንጨት ምሰሶዎች
7,000
የኮንክሪት ምሰሶዎች ማምረት
10.
1,500 ለሚሆኑ የኮርፖሬሽኑ ተሸከርካሪዎች የቀላል ፤የመካከለኛና የከባድ
ጥገና አገልግሎት በመስጠት የኮርፖሬሽኑን ዋና ዋና የሥራ ሂደቶች መደገፍ
11. የኮርፖሬሽኑን የወደፊት አቅጣጫ የሚያሳይ በስትራተጂክ፣ በፓወር
ሲስተም እና በሪሰርችና ዲቨሎፕመንት ላይ ተመስርቶ የተከናወነ ሥራ
ማካሄድ
የሁለትዮሽ የመረጃ ማዕከል ሆኖ የሚያገለግል የኮርፖሬሽኑን ብሎም የሀገሪቱን
ገጽታ ግንባታ ማከናወን
የጀነሬሽን ኦፐሬሽን ሥራዎች
1. የሶር ኃይል ማመንጫ ማስፋፊያና መልሶ ግንባታ
2. የመልካ ዋከና ኃይል ማመንጫ ጣቢያ የመልሶ ግንባታ
3. ሥራቸው ወደቀጣይ በጀት ዓመት የተላለፉትን በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ
ኮርፖሬሽን የተጠገኑ በድሬዳዋ፣ በአዋሽ 7 ኪሎና በቃሊቲ የሚገኙ የተበላሹ
የዲዝል ጀነሬተሮች
4. የሚቀርበውን የኃይል ጥያቄ ለመመለስ የሚያስችል ከተያያዙት ኃይል ማንጫ
ጣቢያዎች 6598.47 ጌዋት ሠዓት እና ካልተያዙት ጣቢያዎች 15.99 ጌዋሰ
የተመነጨ የኤሌክትሪክ ኃይል